Good News Shonga Enterprise is Officially Launched

Shonga Enterprise Good News Shonga Enterprise is Officially Launched በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ “ሾንጋ ኢንተርፕራይዝ” በይፋ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ ጥር 26/2014ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ተያያዥ በሆነ መልኩ ገቢ ሊያገኙ የሚችሉባቸውን አገልግሎቶች በመስጠት የገቢ አቅማቸውን ለማሳደግ፤ ከሚገኘውም ገቢ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጋር ተያያዥ ሥራዎችን ለመስራት እንዲያስችል በገቢ ማስገኛ መመሪያ ቁ/04/2012 መሰረት የገቢ ማስገኛ ድርጅቶች ይቋቋማሉ፡፡በመሆኑም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የገቢ ማመንጫ ክፍሉን በዳይሬክቶሬት ደረጃ ካቋቋመበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በተልዕኳቸው በመለየትና የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ አንቀፅ 64 በሚፈቅደው መሰረት ገቢ ማስገኛ ድርጅት ለመመስረት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሰፊ የህግ፣ የአዋጭነት ጥናት፣ የዝግጅትና በሙከራ ደረጃ ቢሆንም የማምረት ስራ ሲያከናውን መቆየቱም ታውቋል፡፡ ይህን ሂደት በዋናነት በመምራት በሶስቱም ግቢዎች ደረጃ የአገልግሎት ስራዎችን የሚያከናውን የገቢ ማመንጫና በአገሪቱ የንግድ ህግ መሰረት የሚሰራውን የገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዝ ለያይቶ ለማደራጀት ሃላፊነት የተሰጠው ዳይሬክቶሬቱ አያሌ ተግባራትን ሲያካሂድ ቆይቶ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ የገቢ ማስገኛ ድርጅቱን እውን ለማድረግ ሲካሄድ የነበረውን የመተዳደሪያ ደንብ፣ የሰው ሃይል መነሻ መዋቅርንና፣ የአዋጪነት ጥናቶች ዝግጅትን ገምግሞ በማፅደቅ ለኢንተርፕረይዙ መነሻ 55 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሰጥቷል፡፡የኢንተርፕራይዙን የሚመራ ስራ አስኪያጅ መረጣም አድርጓል፡፡ በመጨረሻም የእስካሁኑን ተግባር በባለቤትነት ዘርፍ ሲመሩ በነበሩት የገቢ ማመንጫ ዳይሬክተር አቶ ተስፋው ይታየውና በሾንጋ ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ታዬ መካከል የርክክብ ተግባር በማስፈፀም የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ “ሾንጋ ኢንተርፕራይዝ” ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Mizan-Tepi UniversityLight of the green Valley!

Shonga Enterprise Good News Shonga Enterprise is Officially Launched

Leave a Reply