ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመፈለግ ያጠፉ የነበረውን የትምህርት ጊዜ በማቃለል ከፍተኛ ጥቅም ያላቸውን ሱቆች በዛሬው እለት ለሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አስረክቧል፡፡ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ባስተላለፍት መልዕክት ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የዛሬው ስራ ግን ዩኒቨርሲቲውንና ማህበረሰቡን በተለይም ወጣቱን ይበልጥ የሚያቀራርብ ሲሉ ተናግረዋል፡፡