Mizan-Tepi University
       Light of the green valley!

Tepi Fresh Students Welcome
 
» Materials for 2019 year » Page 2
Sort articles by: date | rating | read | title

Author: Admin dated 20-11-2019, 12:47
 • Dislike
 • 0
 • Like
በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና የአስተዳደር ሀላፊዎች ምርጫ ሹመት ምደባ ለመደንገግ በወጣው መመሪያ 002/2011 መሰረት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ በ39ኛው መደበኛ ስብሰባው የ3 ምክትል ፕሬዝዳንቶችን የውድድር ግምገማ ውጤት አጸደቀ፡፡ በዚህም መሰረት ዶ/ር አብዮት አስረስ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር ሱሌይማን አብዱልቃድር የአስተዳደርና ተማሪዎች ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ዶ/ር ተመስገን መኩሪያን የቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡና ከህዳር 8/2012 ዓ/ም ጀምሮ በተመደቡበት የሀላፊነት ቦታ የተጣለባቸውን ሀላፊነት ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘበብ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ ከአደራ ጭምር በማሳሰብ ምደባ መስጠቱ ታውቋል ፡፡ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለምክትል ፕሬዝዳንቶቹ እንኳን ደስ ያላችሁ እያለ መልካም የስራ ዘመን ይመኛል፡፡
የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ለተደራጁ 20 ማህበራት አገልግሎት እዲውል ያስገነባቸውን 21 ሼዶች/ሱቆችን/ አስረከበ ፡፡

Author: Admin dated 15-11-2019, 09:49
 • Dislike
 • 0
 • Like
ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመፈለግ ያጠፉ የነበረውን የትምህርት ጊዜ በማቃለል ከፍተኛ ጥቅም ያላቸውን ሱቆች በዛሬው እለት ለሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አስረክቧል፡፡ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ባስተላለፍት መልዕክት ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውሰው የዛሬው ስራ ግን ዩኒቨርሲቲውንና ማህበረሰቡን በተለይም ወጣቱን ይበልጥ የሚያቀራርብ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሚ ዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሁለት የምክትል ፕሬዝዳትነት ቦታዎች ላይ ው ድድር ተካሄደ፡፡

Author: Admin dated 15-11-2019, 09:36
 • Dislike
 • 0
 • Like
ጥቅምት 22/2012ዓ/ም
ዩኒቨርሲቲው በአገር አቀፍ ደረጃ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተዘጋጀው የውድድር መስፈርት መሰረት ባወጣው የውድድር ማስታወቂያ ባሉት ሁለት የምክትል ፕሬዝዳንት ቦታዎች ማለትም በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንትነት እና በቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳዳሪዎች ለመወዳደር ባመለከቱት መሰረት በትናንትናው እለት የውድድሩን መስፈርት አሟልተዋል ያላቸውን ተወዳዳዎች አቅርቦ በዩኒቨርሲቲው ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ እና የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስራት አሰፋ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ፣የሴኔት እና ካውንስል አባላት በተገኙበት ብመረጥ አከናውነዋለሁ ያሉትን አጭር ስትራቴጂያዊ እቅድ አቅርበዋል፡፡

በባህላዊ ቅርሶች አስፈላጊነት፣ እንክብካቤና አስተዳደር ዙሪያ የተዘጋጃው የውይይት መድረክ

Author: Admin dated 27-09-2019, 11:14
 • Dislike
 • +1
 • Like
በባህላዊ ቅርሶች አስፈላጊነት፣ እንክብካቤና አስተዳደር ዙሪያ በተዘጋጃው የውይይት መድረክ ላይ
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተዘጋጀው ኪያ ሸኮ-ኖጉ- አመርኛ -እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ተመረቀ፡፡

በሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ት የባህልና ሀገር በቀል እውቀት ጥናትማስተባበሪያ አዘጋጅነት ለአንድ ቀን የሚቆይ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች አስፈላጊነት፣እንክብካቤና አስተዳዳር ላይ ከቤንች ሸኮ ዞን፣ሸካ ዞን፣እንዲሁም ከምዕራብ ኦሞ ዞን የተውጣጡ የዘርፉ ባለሞያዎችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው መምህራን በቅርስና ማንነት፣ጥበቃና አስፈላጊነት ፣በማጃንግ ብሄረሰብ የልጆች አስተዳደግ ላይ የተጠኑ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችን ተመራማሪ መምህራን የተዘጋጀው ‘’ኪያ የሸኮ-ኖጉ -አማርኛ-እንግሊዘኛ’’ መዝገበ ቃላትም ተጠናቆ ተመርቋል፡፡

ለሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች

Author: Admin dated 26-09-2019, 15:08
 • Dislike
 • 0
 • Likeለሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች


ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቅድሚያ ለመላው ተማሪዎቹ እንኳን ለ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን እያለ ተማሪዎቹን የመግቢያ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ያሳውቃል፡፡

ዶ/ር አሚር አማን የኤፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡

Author: Admin dated 20-09-2019, 14:41
 • Dislike
 • 0
 • Like
ዶ/ር አሚር አማን የኤፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡


እንደ ሀገር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የማህበረሰቡን የአገልግሎት ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እየሰራባቸው ከሚገኙት 22 ሆስፒታሎች አንዱ የሆነውን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ ስራዎች ማለትም የጨቅላ ህጻናት እና የእናቶች ማቆያ ማዕከል እንዲሁም አጠቃላይ የሆስፒታሉን የስራ እንቅስቃሴ በባለሞያዎች የተደረገላቸውን ገለጸ አዳምጠዋል፡፡


ክቡር ሚኒስትሩ በያዝነው አመት ስራው ተጠናቆ የሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ለማካተት በማለት እየተገነቡ የሚገኙትን የተማሪዎች ማደሪያ፣ ቤተ-መጽሀፍ፣ መማሪያ ክፍሎች እንዲሁም የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራዎችንም ጎብኝተዋል፡፡
ከመስክ ጉብኝት በኋላ በነበረው አጭር የውይይት ጊዜም አቶ አስራት አሰፋ የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው አስተዳዳር ቦርድ አባል በጤናው ዘርፍ በዞኑ ከሚስተዋኑ አበይት ተግዳሮቶች አበይት የሆኑትን በዝርዝር ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፤ በየደረጃውም የሚገኙ የዘርፉ ሀላፊዎች እና የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው ጉብኝቱን ክቡር ሚኒስትሩ ትኩረት ሰጥተው ማድረጋቸውን አድንቀው ማንሳት በሚገባቸው አበይት ነጥቦች ላይ ሀሳቦቻቸውን ሰንዝረዋል፡፡

Up