የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በ10 ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በ10 ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መንግስት ለከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና የሰጠዉን ትኩረት እና ሌሎች መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም፣ የዉስጥ ደካማ ጎኖችን በመቅረፍ እና ጠንካራ ጎኖቹን የበለጠ በማሳለጥ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካት የተዘጋጀውን የ10 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ሴኔት አዳራሽ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል ውይይት አድርጓል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ በውይይቱ መግቢያ ላይ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደረጀ በጠንካራነቱ የተገመገመው እቅድ በተዋረድ ለዩኒቨርሲቲው አመራርና ፈጻሚ አካላት በማውረድ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ይኸው ውይይት በየዘርፉ ም/ፕሬዚዳንቶች ደረጃ በዝርዝር ውይይት ይደረግና ሁሉም ፈጻሚ አካላት አስተያየት አክለውና አውቀው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ የሚገባ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በመቀጠልም የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕላን፤ ፕሮጀክትና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አቶ ተስፋዬ ደሳለኝ የ10 ዓመቱን ስትራቴጂያዊ እቅድ ዋና ዋና ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በእቅዱ ላይም የተቋሙ መሰረታዊ መረጃዎች፤ የትኩረት አቅጣጫዎች፤ ስትራቴጂክ ዓላማዎች፤ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች፣ የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ስርዓት፤ የስትራቴጂክ ግቦች፣ አመላካቾችና ዒላማዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ካውንስል በርካታ አስተያየቶችንና ተጨማሪ ግብአቶችን በማቅረብ ለቀጣይ አፈጻጸም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Light of the green Valley!

Mizan-Tepi University