የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ሰሞኑን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተመካዮች ጋር ወይይት አደረገ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ባስተላለፉት መልዕክት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቀድሞ በሚታወቅበት የሰላም አንባሳደርነቱ ለማስቀጠል የዞኑ ድጋፍ ዛሬም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎች በፍቅርና በመቻቻል መንፈስ የብሄር እና የሀይማኖት ልዩነት ሳያደርግ ለዘመናት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አቅፎ በመኖር በሚታወቀው የቤንች ሸኮ ዞን ማህበረሰብ ውስጥ እንደመገኘታቸው በወቅታዊ በአንዳንድ የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመረጋጋት ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ እና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያላንዳች ችግር በዋናው ተግባራቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ በማተኮር በሰላም እንዲማሩ አሳስበው መላው የቤንች ሸኮ ዞን ማህበረሰብ ከጎናቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ሙስጠፋ በበኩላቸው የዩኒቨርሲው ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተማሩ መሆኑን ገልጸው የዩኒቨርሲቲው አመራር አሁንም ከአካባቢያችን መንግስና ህዝብ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ፡፡