የ ተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ የምትማሩ ነባር መደበኛ ተመሪዎች የመግቢያ ቀን ጥር 3 እና 4 ሲሆን፣ በ2011 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሚዛን- ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች ማለትም፡-
በ Computer Science
በ Engineering Science
በ Natural And Computational Science
የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነዉ ቴፒ ከተማ በሚገኘዉ ቴፒ ግቢ ጥር 6 እና 7 ስለሆነ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እንገልጻለን ፡፡
ማሳሰብያ፡-
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፡-
10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዉጤት እንዲሁም ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦሪጂናል እና ሶስት ኮፒ፣
ዘጠኝ የቅርብ ጊዜ ሶስት በአራት (3x4) ጉርድ ፎቶግራፍ፣
ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ረጅስትራር ጽ/ቤት