የሸኮ ጎዳ ላሞች ዝርያ ጥበቃና ማሻሻያ ፕሮጀክት በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፡-

የሸኮ ጎዳ ላሞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ማህበረሰባችን ውስጥ በሚፈጠር የአመለካከት ችግር ምክንያት የዝርያውን ቁጡ እና ጉልበተኛ ባህሪ በማየት ከማርባት ይልቅ ለገበያና ለእርድ የመጠቀም ሁኔታዎች በማመዘናችው ምክንያት ዝርያው ቁጥሩ እየተመናመነ በመምጣቱ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የሸኮ ጎዳ ላሞች ዝርያ ጥበቃና ማሻሻያ ፕሮጀክት ከ4 ዓመት በፊት ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡በዚህም መሰረት በቤንች ሸኮ፣ካፋ፣ሸካ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በፕሮጀክቱ ከታቀፉ 7 ማህበራት አስተባባሪዎች ፣ከፌደራልና ከክልል ብዝሀ ህወት ልማት እና የዘርፉ ባለሞያዎች ጋር ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሼቤንች ወረዳ ሲዝ ከተማ በነበረው የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ግምገማ የሸኮ ጎዳ ላሞች ዝርያ አሁን ላይ ከዚህ በፊት በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከተገኘው ቁጥር በ5 ሺህ ልዩነት እድገት ያሳየ ሲሆን በተጠቀሱት ዞኖች በቅርቡ በተደረገ ጥናት ከ7ሺህ የሚልቁ የሸኮ ጎዳ ላሞች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ አንድ የጥበቃና ማሻሻ ማዕከል ያቋቋመ ሲሆን ዝርያውን ከጥፋት ለመታደግ በሸኮ ጎዳ ኮርማ ላሞቻቸውን ለሚያስጠቁ ግለሰቦችና ማህበራትም ማበረታቻ ይሰጣል፡፡
ከሀገር ውስጥ ዝርያዎች የሸኮ ጎዳ ዝርያ በወተት ምርቱና ለእርሻ ስራ ባለው ከፍተኛ ጉልበት የተሻለ እና ውጤታማ ከመሆኑም በላይ በተፈጥሮ የገንዲ በሽታን በመቋቋም ጭምር የሚታወቅ ስለመሆኑ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት