Mizan-Tepi University
       Light of the green valley!

Tepi Fresh Students Welcome
 
» » Page 3
Sort articles by: date | rating | read | title

በ ICT ዘርፍ ለተደራጁ ኢንኩቤቲ ተማሪዎች በኔትዎርክ ዝርጋታ፣ በሶፍት ዌር ልማት ፣ በቢሮ ማሽኖች ጥገና ፣በኢንተርፕርነርሺፕ እና በቢዝነስ ፕላን / ዕቅድ / አዘገጃጀት ዙሪያ የተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ፡፡

Author: Admin dated 30-05-2019, 11:00
 • Dislike
 • +1
 • Like
የደቡብ /ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የግል ስራ ፈጠራ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በ ICT ዘርፍ ለተደራጁ ኢንኩቤቲ ተማሪዎች በኔትዎርክ ዝርጋታ፣ በሶፍት ዌር ልማት ፣ በቢሮ ማሽኖች ጥገና ፣በኢንተርፕርነርሺፕ እና በቢዝነስ ፕላን / ዕቅድ / አዘገጃጀት ዙሪያ የተግባር ተኮር ስልጠና ሰጠ፡፡ ይህ ስልጠና ተማሪዎች በስራ ዓለም በሚሰማሩበት ወቅት በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በተግባር ላይ በተመሰረተ ስልጠና ማስደገፍ መቻላቸው አሁን ላይ የተሻለ ውጤታማ በማድረግ በመስኩም ጥሩ ተወዳዳሪ ምሩቃን ያደርጋቸዋልም ተብሏል፡፡እነዚህ ሰልጣኞች ከዩኒቨርሲቲው ተመርቀው ከመውጣታቸው አስቀድሞ የሚሰጣቸውን ስልጠና በመጠቀም ወደ ሌሎቹ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች በማካፈል ውጤታማ ስራ መስራት የሚያስችላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ በጥቃቅን ምክንያቶች አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ኮምቲተሮችን ባገኙት እውቀት ተጠቅመው ለአገልግሎት እንዲውሉ በማስቻል በቆይታቸው ለዩኒቨርሲቲው ቀላል የማይባል አስተዋጽዎ ሊያበrክቱ እንደሚያስችላቸውም ተብራርቷል፡፡

የሸኮ ዳልጋ ከብት ንዑስ ዝርያ ጥበቃና ማሻሻል መማክርት መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ሰነድን ለማዳበር የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ

Author: Admin dated 5-04-2019, 17:51
 • Dislike
 • +3
 • Like
በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 20 ቀን 2011ዓ.ም የተደረገውን የውይይት መድረክ ያስተባበሩት በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብረሀም አሰፋ እንዳሉት የሸኮ ዳልጋ ከብት ንዑስ ዝርያ ጥበቃና ማሻሻል መማክርት ማቋቋም ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ የሸኮ ዳልጋ ከብት ንዑስ ዝርያ ጥበቃ፣ዘለቂታዊ አጠቃቀምና የምርምር ሥራዎችን በመደገፍ ዙሪያ የሚሰሩ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ለማሰባሰብና በንኡስ ዝርያው ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ሥራዎችን በቅንጅት ማከናወን እንዲቻል ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ አብረሀም ገለጻ የሸኮ ዳልጋ ከብት ዝርያ ቁጥር በመናመን ላይ የነበረ ዝርያ የነበር ቢሆንም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በተሰራው ውጤታማ ሥራ ቁጥሩ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸው ወደ ትክክለኛ ወይም ወደሚፈለገው ቁጥር እንዲደርስ ለማድረግ የዚህ መማክርት መቋቋም እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም የቴፒ ጊቢ ተማሪዎች ቅበላ

Author: Admin dated 11-01-2019, 18:35
 • Dislike
 • +2
 • Like
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቴፒ ግቢ በ2011 ዓ/ም በአንዳንድ አካባቢያዊ ምክንያቶች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የዘገየ ቢሆንም ከ4300 በላይ ነባር ተማሪዎችንና 2183 የሚሆኑ ከፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከጥር 3 ጀምሮ በመቀበል ላይ ይገኛል ፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም የቴፒ ጊቢ ተማሪዎች ቅበላ

የ ተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

Author: Admin dated 8-11-2018, 15:43
 • Dislike
 • +8
 • Like
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ግቢ (ሚዛን) የምትማሩ ነባር መደበኛ ተመሪዎች የመግቢያ ቀን ህዳር 6 እና 7 ሲሆን፣ በ2011 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሚዛን- ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች ማለትም፡-
በ Business and Economics
በ LAW
በ Medicine
በ Public Health Officer
በ Other Health Science
በ Other Social Science and Humanities
በ Other Agriculture and Natural Resource

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም ተማሪዎች አቀባባል ሁኔታ

Author: Admin dated 3-11-2018, 18:00
በተለያዩ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎችሀሰተኛ አሉባልታ ስለ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም ተማሪዎች አቀባባል ሁኔታ እየተነገረ ቢሆንም ተማሪዎችን እንዴት ባማረ መልኩ መቀበል ይቻላል ? እንዴትስ የዩኒቨርሲቲው የሶስቱም ካምፓስ (የዋናው ግቢ ፣ ቴፒ ግቢ እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግቢ ) ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት በሰላማዊ መልኩ መውሰድ ይችላሉ ?

Author: Admin dated 2-10-2018, 22:53
ለሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዳዲስ ተማሪዎች በሙሉ ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 21 እና 22 የነበረ ቢሆንም በት/ት ሚኒስቴር በተዘጋጀው አዲሱ የት/ት የፍኖተ-ካርታ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ጋር የፕሮገራም መደራረብ በመከሰቱ ላልተወሱ ቀናት መራዘሙን በቴሌቪዥን ጭምር ያሳወቅን ቢሆንም በአንዳንድ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የ2011 የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 2 እና 3 /2011 መሆኑን እየገለፁ ሲሆን መረጃው ሀሰተኛ እና ትክክለኛ የዩኒቨርሲቲው መረጃ አለመሆኑን እያሳወቀን የዪኒቨርሲቲያችን የሁለቱም (የዋናው እና ቴፒ) ካምፓሶች ተማሪዎች ትክክለኛው ቀኑን በEBC ፣ የዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት (www.mtu.edu.et) እንዲሁም በፌስቡክ አካውንት ይፍ እስከሚደረግ በሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው የመቀበያ ወቅት ቀድማችሁ ጉዞ እንዳትጀምሩ እና ላልተፈለገ ወጪ እንዳትዳረጉ ለማሳሰብ እንወዳለን

Up