Mizan-Tepi University
       Light of the green valley!

Tepi Fresh Students Welcome
 
» Office of Gender and Diversity Directorate

Office of Gender and Diversity Directorate

የጽ/ቤቱ ዓላማ ፣ተልዕኮና ራዕይ

-የጽ/ቤቱ ዓላማ ፣

- ተወዳዳሪ የሆኑ ብቃትና ችሎታ ያላቸዉን ሴት ባለሞያዎችን ማፍራት ፣

- የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ችግር በመፍታት አቅማቸዉን ማጎልበት ፣

- ለሴት ተማሪዎች ምቹ የመማርና ማስተማር አካባቢን መፍጠር ፣

- ሴት መምህራን በጥናት ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች እንዲሳተፉ ማስቻል ፣

- የፆታ እኩልነት በዩኒቨርስቲዉ እንዲሰፍን ማድረግ ፣

-የጽ/ቤቱ ተልዕኮ ፣

- በራሳቸዉ የሚተማመኑና በትምህርት ተፎካካሪ የሆኑ ሴት ተማሪዎችን ማፍራት ፣

- የሴት ተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ መቀነስ ፣

- የፃታ እኩልነትን በዩኒቨርስቲዉ ማስፈን ፣

- ሴቶች በዉሳኔ ሰጪ አመራር ቦታዎች እንዲመጡ ማስቻል፣

-የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣

- ተወዳዳሪ የሆኑ ብቁና ችሎታ ያላቸዉን ሴቶች በዩኒቨርስቲዉ ፈርተዉ ማየት ፡፡

. በጽ/ቤቱ የሚከናወኑ ዋና-ዋና ተግባራት ፣

. ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም በማዘጋጀት ስለ ስራሂደቱ ፣ ስለ ዩኒቨርስቲዉና ስለ አካባቢዉ ምንነት ማስተዋወቅ፣

. ሴት ተማሪዎች በራስ የመተማመን ብቃትን እንዲያዳብሩ በፆታዊ ትንኮሳ፣ በስርዓተ-ፆታ ሚኒስትሪሚንግ፣በስነ-ተዋልዶ ጤና፣ በህይወት ክህሎት፣ በአጠናን ስልት፣በእንግልዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ፣ በስራ ፈጠራና በመሳሰሉት የክህሎት ማዳበሪያ ጉዳዬች ላይ ስልጠና መስጠት፣

. በተለያዩ ጉዳዬች ላይ ለተማሪዎች የምክር አገልግሎት መስጠት ፣

. ፆታዊ ትንኮሳን መከላከልና ተፈፅሞ ሲገኝም አስፈላጊዉን ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ፣

. ከዩኒቨርስቲዉና ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አካል ጉዳተኞች ፣ የኢኮነሚ ችግር ያለባቸዉ ሴቶችና ልዩ ድግፍ የሚሹ ተማሪዎችን በመለየት የሚረዱበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት ፣

. በኢኮነሚ ችግር ወደ ቤተሰብ መሄድ ያልቻሉ ተማሪዎችን በመለየት በዩኒቨርስቲዉ እንዲቆዩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣

. ሴት ተማሪዎች በተጓዳኝ ትምህርቶች እንደ ሰብዓዊ መብት ባሉ አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ አቅማቸዉን ከፍ ማድረግ ፣

. የቢግ ሲስተርስና የእርስ-በርስ የልምድ ልዉዉጦችን በማድረግ ተማሪዎች እየተዝናኑ ዕዉቀትን በመጨበጥ ጥሩ ተሞኩሮዎቻቸዉን እንዲቀስሙና አርአያነታቸዉን እንዲከተሉ ማበረታታት፣

. የማጠናከሪያ የቲቶሪያል ትምህርት እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና አሰጣጡን መከታተል ፣

. የሴቶች የትምህርትና የፍትህ ፎረምን ማካሄድ፣

. የሴት ተማሪዎች፣መምህራንና ሰራተኞች ማህበርን ማጠናከር፣

. ሴት መምህራንና ተማሪዎች በጥናትና ምርምር እንዲሳተፉ ማበረታታት ፣

. የተሸለ ጥሩ ዉጤት ያስመዘገቡ የዩኒቨርስቲዉና የአካባቢዉ የመሰናዶ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ወዘተ ሲሆን ፡-

- በጽ/ቤታችን በመምጣት እነዚህን ከላይ የተገለፁትን ግልጋሎቶች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ . ስ/ቁ - 0471350093

. ከእያንዳንዷ ልማት ስኬት በስተጀርባ ጠንካራ የልማት አጋር ሴት አለች !!!

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሚዛን ካምፓስ ስርዓተ-ፆታ ጽ/ቤት.በ2008 ዓ/ም በ9 ወር የስራ ጊዜ ዉስጥ በጽ/ቤቱ የተከናወኑ ዋና-ዋና ተግባራት ፣

1. የሴት ተማሪዎችን ማህበር ከማጠናከር አንፃር፣

-የሴት ተማሪዎች ማህበር ተቋቋማል ፣ ተመራቂ የሆኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት በአዲስ አባላት የመተካት ስራ ተከናዉኗል፣ ለስራዉ አገልግሎት እንዲሆን ቢሮ የተመቻቸ ሲሆን ኮሚፒተርና የጽ/ት መሳሪያዎች እንዲያገኙ ተደርጓል ፣

-የማህበሩ የስራ አስፈፃሚ አባላት ከቴፒ ካምፓስ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የልምድ ልዉዉጥ ተደርጓል ፣

- Handout ለማድረግ አቅም ያጡ ተማሪዎችን ኮሌጆች ከስርዓተ-ፃታ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የመለየቱን ስራ ያከናወኑ ሲሆን ድጋፉ እዚያዉ በኮሌጁ ፎቶ ኮፒ ኖሮ እንዲሰጥ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ተደርጓል ፡፡

-ማህበሩ ለስራ እንቅስቃሴ የሚሆነዉን ገንዘብ ከአባላቱ በየወሩ 0.50 ( ሃምሳ ሳንቲም) እየሰበሰበ ሲገኝ በ9 ወሩ 325.00 (ሶስት መቶ ሃያ አምስት )ብር ተሰብስቦ በተከፈተዉ የማህበሩ የባንክ አካዎንት ገቢ ሆናል ፡፡

-ማህበሩ ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ መድረኮችን በማዘጋጀት እየተዝናኑ እንዲማማሩ ያደረገ ሲሆን ለዝግጅቱም ከላይ ከሰበሰበዉ ብር ላይ 200.00(ሁለት መቶ) ብር ለዝግጅቱ መስተንግዶነት አዉላል፡፡

-ለተማሪዉ ምቹ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ በሴት ተማሪዎች ዶርም አካባቢ የተማሪ ላወንጅና የቁንጅና ሳሎኖች ተከፍተዉ ተማሪዉ በቅርቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እዲሆን ያስቻለዉ ሲሆን በዶርም ዉስጥም የቲቪ ሩም ተመቻችቶለታል ፡፡

2. የፀረ-ፆታዊ ትንኮሳ ህጉን ተግባራዊ ከማድረግና ሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት አስቀድሞ ከመከላከል አንፃር ፣

. አስቀድሞ ከመከላከል አንፃር ፣

-በዩኒቨርስቲዉ የፀረ-ፆታዊ ህጉ ላይ ለተማሪዎችና ለድጋፍ ሰጪ አስተዳደር ሰራተኞች ጽ/ቤቱ ከዩኒቨርስቲዉ የህግ ክፍል ጋር በመተባበር ስልጠናዉን ሰጥቷል ፡፡

-ፆታዊ ጥቃት ከሰብዓዊ መብት አንፃር እንዲታይ በዩኒቨርስቲዉ ዉስጥ በሰብዓዊ መብት ክበብ በኩል በአቻ ለአቻ ፕሮገግራም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱ ተሰጥቷል ፡፡

-በሴት ተማሪዎች ማህበር በኩል የፓናል ዲስከሽን በማዘጋጀት ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዉ ፆታዊ ጥቃት ሲያጋጥማቸዉ ለማንና እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸዉ ተገልፆላቸዋል ፡፡

-ዓለምዓቀፍ የነጭ ሪቫን ቀን ፆታዊ ጥቃትን በጋራ እንከላከል በሚል መፈክር በዩኒቨርስቲያችን በተከበረ ወቅት ወንዶች በሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ፆታዊ ጥቃትን በማዉገዝ በበዓሉ ላይ ነጭ ሪቫን አድርጎ በመገኘት አጋርነታቸዉን ገልጸዋል ፡፡

. ትንኮሳዉ ተካሄዶ(ተፈፅሞ) ሲገኝ ፣

-በፀረ- ትንኮሳዉ ህጉ፣በተማሪዎች የዲስፕሊን ደንብ፣በሰራተኛ የዲስፕሊን ህግና ለመምህራን በሴኔት ሊጅስሌሽን ህጉ ላይ ተመስርቶ እንደተፈፀመ የጥፋቱ ዓይነትና ክብደት ተመጣጣኝ የቅጣት እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ከዚህ አንፃር በትምህርት ዘመኑ በሚዛን ካምፓስ-3 ይኸዉም (2 ተማሪ ከተማሪ ፣ 1 መምህር ከተማሪ)፣ በቴፒ ካምፓስ 2 ይኸዉም ( 1 አሰተዳደር ሰራተኛ ከተማሪ፣ 1 መምህር ከተማሪ) በድምሩ 5 ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን በሚዛን ተማሪ ከተማሪ ጋር የደረሰዉ 2 ፆታዊ ትንኮሳ በመጨረሻ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ፣በመምህሩ የደረሰዉ ፆታዊ ጥቃት የ3 ወር ደመወዝ ከመጨረሻ ከባድ ማስጠንቀቂያ ጋር ሲሰጥ ፣በቴፒ ካምፓስ ለተፈፀመዉ ጥቃት ፈፃሚዉ የአስተዳደር ሰራተኛ ስራዉን

በመልቀቅ ከቦታዉ በመሰወሩ ክሱ በዉጭ በኩል ለዓቃቤ ህግ ቀርቡ ጉዳዩ በክትትል ላይ ሲገኝ በመምህሩ የደረሰዉ ጥቃት በሴኔት ህጉ መሰረት ጉዳዩን ለማየት ዝግጅቱ ተጠናቋል ፡፡

3. የኢኮነሚ ችግርና የተማሪዎችን የትምህርት ተግዳሮቶች ከመፍታት አንፃር ፣

-ጽ/ቤቱ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ እንዲዘልቁ ከጀንደር ጋር የተያያዙ ጉዳዩችን የሚኒስተትሪሚንግ አገልግሎትን የሰጠ ሲሆን ከጋይዳንስና ካዉንስሊንግ ጋር በመተባበርም በሶሻልና በአካዳሚካዊ ችግሮች ዙሪያ ላይ የምክር አገልግሎትን ሰጥቷል ፡፡

-ተማሪዎች የላቀ ዉጤት እንዲያስመዘግቡና ትምህርታቸዉን በአግባቡ እንዲከታተሉ በመምህራን በኩል የምክር አገልግሎት የተካሄደ ሲሆን ይኸዉም ፡-

- መምህራን በተመካሪነት የተመደበላቸዉን ተማሪዎች ስም በሚታይ ቦታ ለተማሪዎች በመለጠፍ ወይም በትምህርት ክፍሉ ተጠሪ አማካኝነት ተማሪዎች አማካሪያቸዉን እንዲያዉቁ ተደርጓል፡፡

- አመካሪ መምህራን የሚገኙበትን ሰዓት ለተመካሪዎቻቸዉ እንዲያሳዉቁ ከተደረገና የማማከሪያ ሰዓት ከተገለፀ በኃላ በዩኒቨርስቲዉ በሚገኙ ኮሌጆች ስር ያሉ የትምህርት ክፍሎች መምህራን ለተማሪዎች ፡- በትምህርትና ተያያዥ ጉዳዬች ላይ ፣ በህይወት ክህሎት ስልጠና ስለአጠናን ስልት ፣ ስለበራስ መተማመን ስለ ሰዓት አጠቃቀም እና ተማሪዎች ገጠመኝ ባሉት ችግር ላይ እንዲያማክሩ ተደርጓል ፡፡ይህ በመምህራን

በራስ ፍቃድና ተነሳሽነት ሲካሄድ የነበረዉ ድጋፍ እና ከትምህረት ክፍል መረጣ እስከ ምረቃ ድረስ እየተሰጠ ያለዉ ልዩ የምክር አገልግሎት ፡-

-ተማሪዎች በጊዚያዊ ችግር ትምህርታቸዉን እንዳያቋርጡ፣

-በህመም አሊያም በሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ትምህርታቸዉን የሚያቋርጡበት አጋጣሚ ቢከሰት አስፈላጊ ሂደቶችን በአማካሪያቸዉ አጋዥነት እንዲያገኙ፣

-ከመደበኛ ትምህርት ዉጭ የሚሟሯቸዉ ወይም መማር የሚገባቸዉ ኮርሶች ቢኖሩ በአማካሪያቸዉ አማካኝነት ግልፅ እንዲሆንላቸዉ ሲደረግ በተለይ ሴት ተማሪዎች ማንኛዉንም ችግሮች ለመግለፅና መፍትሔ ለማግኘት አስችላቸዋል ፡፡

-በወቅታዊና እና ተማሪዎች ገጠመኝ ባሉት ችግር ላይ እነሱ በመረጣቸዉ ርዕስ ላይ በዶርም Tv Room ላይ የፓናል ዲስከሸን ተካሂዷል ፡፡

-የኢኮነሚ ችግር ላጋጠማቸዉ 446 ተማሪዎች በወር 150.00(አንድ መቶ ሃምሳ ብር) እያገኙ በጥቅሉ ብር 602100.00 ( ስድስት መቶ ሁለት ሺህ አንድ መቶ) ብር በዩኒቨርስቲዉ ድጋፍ እንዲረዱ በሴኔት አስወስኖ ተግባራዊ እንዲደረግ አድርጓል ፡፡ ይህም ድጋፍ በመሃል ደብተርና እስክብሪቶሲያልቅባቸዉ ሳይጨናነቁ ለመተካት አቅምን የፈጠረላቸዉ ፣ጥቂትም ቢሆን የፎቶ ኮፒ ወጪያቸዉን በመጠኑም ቢሆን በመሸፈን በዉስን መልኩም ችግሮቻቸዉን የቀረፈ ሲሆን በዚህ ምክንያት የሚከሰተዉን መጠነ ማቋረጥን ለመቀነስ ትልቅ እገዛ ከማድረጉም ባሻገር ተማሪዎች ተረጋግተዉ እንዲማሩ የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል

-ከላይ ከተጠቀሱት ተማሪዎች ዉጭ ሌሎች የኢኮነሚ ድጋፍ የሚሹ 45 ተማሪዎች ከትምህርት ክ/ጊዚቸዉ ዉጭ የጥናትም ጊዚያቸዉን ባልነካ መልኩ በመረጣቸዉ ቀንና ጊዚያት በፍቃደኝነት በላይብረሪ በሰርኩሌሽን ስራ ለማገልገል ተመዝግበዉ በወር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር) ድጋፉን በማግኘት ላይ ይገኛሉ ፡፡

-ከላይ ከተጠቀሱት ተማሪዎች ዉጭ ሌሎች የኢኮነሚ እርዳታዉን በማሻት የተመዘገቡ ቢሆንም በመለየቱ ስራ ያልተካተቱ ተማሪዎችን ለመርዳት የፎቶ ኮፒ እገዛ በጽ/ቤቱና በየትምህርት ክፍላቸዉ በኩል እንዲያገኙ ተደርጓል ፡፡

-ከየኮሌጁ የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ለ24 ተማሪዎች 19200.00(አስራ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ) ብር በዩኒቨርስቲዉ ማኔጅምት በማስወሰን የገንዘብ ሽልማቱ ድጋፍ ተደርጓል ፡፡

4. ሴቶችን ለማበረታታት ከተካሄዱየትምህርት ፎረሞች፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና ከተሰጡ የማጠናከሪያ የቲቶሪያል ትምህርቶች አንፃር ፣

- ለተማሪዎች በስነ-ተዋልዶ ጤና፣ በተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት አጠቃቀምና ቁጥጥር፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ እና በፀረ-ፆታዊ ትንኮሳ ህጉ እና በህይወት ክህሎት ስልጠና ስለበራስ መተማመን፣ስለ የአጠናን ስልትና ስለ ሰዓት አጠቃቀም ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

-ከተማሪዎች ጋር የጠበቀ የዕለት-ተዕለት ግንኝነት ላላቸዉ ለአስተዳደር ሰራተኞች ይኸዉም ለፕሮክተሮች፣ለጥበቃ ፖሊሶችና ለላይብረሪ ሰራተኖች በፀረ-ፆታዊ ትንኮሳ ህጉ እና በስነ-ተዋልዶ ጤና ላይ ስልጠናዉ ተስጥቷል ፡፡

-በተማሪዎች መካከል ያለዉን የዉጤት ልዩነትን ለማጥበብ የማጠናከሪያ የቲቶሪያል የትምህርት እገዛ ከኮሌጆችና ከዲፓርትመንቶች ጋር በመተባበር ከ2.5 በታች ለሴቶች፣ ከ2.2 በታች ለወንዶች ሆኖ ይህንኑ ዝቅተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሶስት ኮርሶችን እንዲመርጡ በማድረግ ተማሪዉ እገዛዉን በመረጣቸዉ ኮርሶች ላይ ትምህርቱ እንዲያገኝ ተደርጓል ፡፡-በዩኒቨርስቲያችን የሴቶች ትምህርት ፎረም በአዲስ መልክ ተቋቁማል ፡፡ ፎረሙ ሲቋቋም በትምህርት ሚኒስተር የመጣዉን ሰነድ መሰረት በማድረግ የራሱን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተወሰነ ማሻሻያ በማድረግ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች፣መምህራን፣የአስተዳደር ሰራተኞችና የሴቶች አደረጃጀት አመራር አካላት ፎረም መመሪያ ቁጥር1/2008 በሚል ሰነዱን ቀርፆ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዕቅዱም መሰረት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ፡፡

- የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ በአርአያነት እንዲቀርቡና እንዲሸለሙ ተደርጓል ፡፡

- የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን መልካም ተሞኩሮ ሌሎች ተማሪዎች በመዉሰድ ይከተሉ ዘንድ ፎቶቸዉ በዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በአርአያነት እንዲለጠፍ ተደርጓል ፡፡

-ሴት መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ወደ አመራርነት ቦታ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት 5 ሴት መምህራን፣ 3 ሴት የአስተዳደር ሰራተኞች በድምሩ 8 ሴቶቸ በዉሳኔ ሰጪ የአመራር ቦታዎች ላይ እንዲቀመጡ ተደርጓል ፡፡

-ሴት መምህራን በጥናት ምርምር እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት 10 ሴት መምህራን በጥናትና ምርምር ተሳትፈዋል ፡፡

-ሶስተኛ ዲግሪ ባላቸዉ መምህራንና ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸዉ ሴት መምህራን መካከል የሜንተር-ሜንቲ ግንኙነት ተፈጥሮ ሴት መምህራን ወደ ሶስተኛ ዲግሪ ከመሄዳቸዉ በፊት ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ሁኔታ በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ስራዉ ሲከናወን ወደ ሌሎች ኮሌጆችም ይህ መልካም ተሞኩሮ እንዲሰፋ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል ፡፡

5. ከማህበረሰብ አገልግሎትና ድጋፍ አንፃር፣

-ሴት መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ እንዲሳተፉ የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት 10 ሴት መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ ተሳትፈዋል ፡፡

-በሚዛን ማረሚያ ተቋም ዉስጥ ለሚገኙ ሴት ታራሚዎች በስርዓተ-ፆታ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል ፡፡

-በሚዛን ማረሚያ ተቋም ዉስጥ ለሚገኙ አረጋዊያንና ሴት የህግ ታራሚዎች ላለባቸዉ የመኝታ ችግር ማቃለያ ይሆን ዘንድ ያገለገለ 170 የተማሪዎች ፍራሽ በልገሳ ተሰጥቷል ፡፡

-የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ በሚዛን መሰናዶ ት/ቤት ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት ድጋፍ ተደርጓል ፡፡ ለተማሪዎች በስርዓተ-ፆታ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል ፡፡

. የጽ/ቤቱ የቢሮ ቁጥር ፡- 48
. የጽ/ቤቱ ስልክ ቁጥር ፡- 0471350093
. ኢ-ሜይል ፡- ashrutemam 14@gmail.com
. የሃላፊዉ ስም ፡- መ/ር/ት አሽረቃ ተማም
. የሃላፊዉ ስልክ ቁጥር ፡- 0910682596

መ/ር/ት አሽረǓ(Director )