HR Development

Human Resourece Devevelopment Directorate

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርስቲ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2012 ዓ.ም ማጠናቀቂያ ላይ በክፍሉ የሥራ ድርሻ መሠረት በስትራቲጂያዊና ፣ የዘመነ አኳኋን ጥራትና ቅልጥፍና ያለው አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን የሰው ኃብት ዕድገትና ልማት ለማረጋገጥ በመጣር ሞዴል ሆኖ መገኘትና እመርታዊ ለውጥ ማምጣት እንዲሁም አስተማማኝ የሆነና በየዘርፉ የተቀናበረ የሰው ኃይል መረጃ በማንኛውም ጊዜ አደራጅቶ መገኘት በዚህም የዩኒቨርስቲውን የአሠራር ደረጃ ወደ ከፍታ ማምጣት፡፡

ተልዕኮ

የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርስቲውን መምህራንና ሠራተኞች ሁሉ የሚደግፍና የሚያለማ በሥራቸው ቀጣይነታቸውን የሚያረጋግጥ የሥራ ሁኔታን መፍጠር፣ ማበረታታትና መደገፍ ዋና ተልዕኮው ነው ይህንንም በዕውቀት በተደራሽነትና በሙያዊ ክህሎት ላይ በመመስረት በሠራተኞች መስተጋብር ፣ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ፣ ማበረታቻ ፣ በምልመላና መረጣ በዕድገት መሠላል ረገድ ተስማሚና የሃገሪቱ አዋጆች መመሪያና ደንቦችን ያገናዘበ የማስፈፀሚያ የውስጥ መመሪያ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ማዋል፡፡

ስትራቲጂያዊ አመራርን ፣ ታማኝነትንና ሃቀኝነትን የቅንጅት ሥራን በአጠቃላይም የፐብሊክ ሰርቫንቱን ሙያዊ የሥነ ምግባር መርሆዎች በማረጋገጥ የዩኒቨርስቲያችንን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት መጣር፡፡

( Tel – 0473360354 – 0473360299 – 0473360151 – 0473360159

Fax – 0473360400

Office No 27

E-mail-gezahegntm52@gmail.com

ክፍሉ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት፤

አጠቃላይ የሰው ኃይል ዕቅድ በማዘጋጀት፣

ü የመምህራንና ሠራተኞች ምልመላ መረጣና ቅጥር እንዲሁም ዝውውር መፈፀም፣

ü የመምህራን የሠራተኞች የደረጃ ዕድገትና ጥቅማ ጥቅም ማበረታቻ ማስጠበቅ፣

ü የመምህራንና ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናና ልማት ማከናወን፣

ü የመምህራንና ሠራተኞችን የስራ አፈፃፀም አሞላል ተግባራት መከታተል መደገፍ ሪከርድ መያዝ፣

ü የመምህራንና ሠራተኞችን የዲስፕሊን አፈፃፀምና ቅሬታ አቀራረብ መከታተል፣

ü የደሞዝ ክፍያን መረጃዎች በማደራጀት ለክፍያ መላክ፣መቆጣጠር፣

ü ልዩ ልዩ ዓይነት ፈቃድና ዕረፍቶችን ማስተዳደር፣

ü የመምህራንና ሠራተኞችን የሥራ አካባቢ ደህንነት ማረጋገጥ፤ የጡረታ፣የጤና መድህንና የሥራ ግብር ክፍያና ተያያዥ ሥራዎችን ማከናወን፣

ü የዩኒቨርስቲውን አጠቃላይ የውስጥና የውጭ ግንኙነት የደብዳቤ ልውውጦችና ሌሎች ሰነዶችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ፣ የሠራተኞችን መረጃና ማህደር አደራጅቶ መያዝ፣

ü ልዩ ልዩ መመሪያዎችን አሰባስቦ መያዝና ለግቢው ማህበረሰብ ሁሉ ማስተዋወቅ፣