በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ለሚገኙ የአስተዳር ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የካይዘን ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡ ግንቦት 12/2013 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፡፡በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ለሚገኙ የአስተዳር ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የካይዘን ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ስልጠናው በተለይ ለቢሮ ጸሀፊዎች ፣ መልዕክተኞችና የንብረት ክፍል ሰራተኞች ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው ፡፡ ሰራተኞቹ በንድፈ ሀሳብ የተሰጣቸውን ግንዛቤ በተግባር በማስደገፍ ጭምር የተለያዩ የተግባር ልምምድ ደረጉ ሲሆን በግቢው ውስጥ በተለያዩ የስራ ክፍሎች በተለይ ንብረት ክፍል የሚገኙ ንብረቶችን በካይዘን በማደራጀት ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን የማድረግ ተግባር አከናውነዋል ፡፡
Light of the green Valley!