የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲና አካባቢው ችግኝ ተከላ አካሄዱ።
ሰኔ 9/2013 ዓ/ም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፡፡የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ከአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች፣ በስራ ፈጠራ ሌሎች ተግባራት ስልጠና እንዲያገኙ አድርጎ ለዚሁ የተቀደሰ ዓላማ ወደ ተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ማሰማራቱ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ወጣቶች በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲና አካባቢዋ ከመጡ ወዲህ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በማከናወን ላይ ናቸው ፡፡
በዛሬው እለትም በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥና ከግቢው ውጭ ችግኝ ተክለዋል፡፡ ወጣቶቹ ወደፊትም በሚኖራቸው የ6 ወራት ጊዜ ቆይታ በዩኒቨርሲቲው እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራቸውን መስጠት እንደሚቀጥሉ ታውቋል ፡፡